በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ብሄራዊ ሳይንስ ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ፣ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ እና ስታርትአፕ አዋጅ ላይ የተዘጋጀ ወርክሾፕ ተካሄደ፡፡
በመርክሾፑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የተከበሩ ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና እንዳሉት ይህ መድረክ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ወርክሾፕ የትብብር ፍሬያችን የሚታይበት እና የፈጠራ አቅምን የምናጎለብትበት መድረክ እንደሆነ ገልፀው፤ የነገይቱ ኢትዮጵያ የምትፈልገው ተመራማሪ ጠያቂ እና ፈጣሪ የሆነ ትውልድ ነው፡፡ይህም በመሆኑ በዚህ ዙሪያ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የረጅም ጊዜ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱንም ክቡር ፕሬዝደንቱ ገልጸዋል፡፡
አክለውም እናንተ ዛሬ እውቅና የምንሰጣችሁ የነገይቱ ኢትዮጵያ ተስፋ የሆናችሁ ተማሪዎቻችን በፈጠራ ስራዎቻችሁ ኢትዮጵያን የምታስቀድሙ ቅድሚያ ለሀገሬ የምትሉ መሆን ይኖርባችኋል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስተር እና የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ይህን አይነት ወርክፖችን ከዩነቨርሲቲዎች ጋር በመሆን የሚያዘጋጅበት ሁለት ዋና ዓላማዎች አሉት፡፡የፈጠራ ክህሎት ያላቸውን ባለተሰጥኦዎችን መርጦና አሰልጥኖ እውቅና መስጠት ይህንን ተከትሎም ሌሎች የእነርሱን አርአያነት በመከተል የተነሳሽነት መንፈስን መፍጠርን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በፈጠራ ክህሎት ዙሪያ በዚህ ዓመት ከሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመስራት ላይ ያለ ሲሆን አንዱ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በእለቱ የወርክሾፑን የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት ደግሞ ክቡር ዶ/ር ባይሳ በዳዳ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን እና ምርምር ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ሲሆኑ በንግግራቸውም መደ በላቡ ዩኒቨርሰቲ እና በለድርሻ አካላት የፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ወጣቶች እንዲያበረታቱና በጋራ መስራት ውጤታማ እንደሚያደርግ ያሰመሩበት ሲሆን ሚኒስተር መስራቤታቸውም ከጎናቸው እንደማይለይ አበራርተዋል፡፡
በዛሬው መድረክ ላለፉት ሰባት ቀናት በተቋሙ ተገኝተው የፈጠራ ክህሎት ውጥነ እቅዶቻቸውን ያቀረቡ ከባሌ ፣ምስራቅ ባል እና ምእራብ አርሲ ዞኖች ስልሳ አምስት ተወዳዳሪዎች መካከል በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባስቀመጠው መመዘኛ መሰረት 35 የሚሆኑት ተመርጠው ስልጠና ከተሰጣቸው መካከል በውድድሩ ላሸነፉት አስር አሸናፊዎች የእውቅና ሰርትፊኬት ከክቡር ሚኒስትሩ፣ ከክቡር ፕሬዝዳንቱ፣ከክቡር ሚኒስትር እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ተበርክቶላቸዋል፡፡
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት
For More Information Use the following links:
Facebook: https://web.facebook.com/MaddaWalabuUniversityPages/
LinkedIn: https://www.linkedin.com/com.../madda-walabu-university-page
Telegram: https://t.me/Maddawalabubot
X/Twitter: https://x.com/MWU_University
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbCT1iYKbYMFSfNxOq1U
E-mail: info@mwu.edu.et
Event Gallery




















