አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) ለመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ለህክምና ላቦራቶሪ የሚዉሉ የተለያዩ የላቦራቶሪ መሣሪያዎችን በእርዳታ አበረከተ።

አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) ለመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ለህክምና ላቦራቶሪ የሚዉሉ የተለያዩ የላቦራቶሪ መሣሪያዎችን በእርዳታ አበረከተ።

Mar 16, 2026

አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) ለመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ከ1.5ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ የህክምና ላቦራቶሪ መሣሪያዎችን በእርዳታ አበረከተ።


ይህ በእርዳታ መልክ የተሰጠው የህክምና ላቦራቶሪ መሳሪያዎች የተለያዩ ሪኤጀንቶችን ለረጅም ጊዜው በ(2-8 °c) አቀዝቅዞ ለመቆየት የሚያገለግል ፍሪጅ (Referegerator)፣ ለታካሚና ለተለያዩ ምርምሮች የሚዉሉ የተለያዩ ናሙናዎችን ለረጅም ዓመታት በ(-80°c)አቀዝቅዞ ለማከማቸት የሚውሉ (Deep Freezer)፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ለምርምርና ለታካሚዎች የሚዉሉ የተለያዩ (Media Steralize) ለማድረግ የሚዉል መሣሪያ እንዲሁም ጎጂ የሚሆኑ ተዋሲያን ለማጥፋት የሚያገለግል መሳሪያ (Auto Clave) እና ለምርምርና ለታካሚዎች ምርመራ የሚያገለግል እንዲሁም የተዋሲያን ዘረመል (RNA) ከናሙና ዉስጥ ለመለየት የሚያገለግሉና ለሆስፒታሉ ከፍተኛዉን አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሳሪያ መሆኑን የገለፁት በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሶስተኛ ድግሪ ዕጩ የሆኑት መ/ር እሸቱ ንጉሴ ናቸው።


በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ተባባሪ ፕሮፌሰር ሙሀመድአማን ማማ እንደገለፁት አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) ከዩኒቨርሲቲያችን ጋር በተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ መሰረት ከ1.5 ሚሊየን በላይ የሚገመተውን የተለያዩ የህክምና ላቦራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ ማድረጉ ለሆስፒታሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ገልፀዉ ይህ በድጋፍ የተገኘዉን መሳሪያ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች በጥንቃቄ በመያዝ ለተገልጋዮች የህክምና አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው ሁሉም የስራ ክፍሎች የመግባቢያ ሰነዶች (MoU) ከተለያዩ የሀገርና የውጭ ሀገር መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ሲፈረም ኃላፊነትን በመውሰድ ለተግባራዊነቱ መትጋት ግድ ይላል፡፡


መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት

For More Information Use the following links:

Facebook: https://web.facebook.com/MaddaWalabuUniversityPages/

LinkedIn: https://www.linkedin.com/com.../madda-walabu-university-page

Telegram: https://t.me/Maddawalabubot

X/Twitter: https://x.com/MWU_University

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbCT1iYKbYMFSfNxOq1U

E-mail: info@mwu.edu.et

Event Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7

Related Articles

View All
አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) ለመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ለህክምና ላቦራቶሪ የሚዉሉ የተለያዩ የላቦራቶሪ መሣሪያዎችን በእርዳታ አበረከተ። | Madawalabu University