መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ከMSH Eliminate Project ጋር በመተባበር በጎባ ማረሚያ ቤት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ነፃ  የሳንባ በሽታ ምርመራ  እየሰጠ ይገኛል።

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ከMSH Eliminate Project ጋር በመተባበር በጎባ ማረሚያ ቤት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ነፃ የሳንባ በሽታ ምርመራ እየሰጠ ይገኛል።

Mar 16, 2026

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ከMSH Eliminate Project ጋር በመተባበር በጎባ ማረሚያ ቤት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ነፃ የሳንባ በሽታ (TB) በዲጂታል X-Ray ማሽን ነፃ የምርመራ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።


በMSH Eliminate Project የባሌ ዞን እና የሮቤ ከተማ የሳንባ በሽታ መከላከል አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደደፎ ባቲ እንደገለፁት በአሁኑ ወቅት እንደ አለም አቀፍ በአመት ከ10,000,000 ህዝብ በላይ እንደ ኢትዮጵያ ደግሞ ከ250,000 ህዝብ በላይ በአንድ አመት ብቻ በሳንባ በሽታ የተያዙ ሲሆን እንደ ኦሮሚያ ከ60,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በዚህ በሽታ የተያዙ መሆኑን ገልፀዉ ለዚህ በሽታ ስርጭት መስፋፋት ዋና ምክንያት የሆነው በበሽታዉ የተያዘ ግለሰብ አየር በተገቢው የማይገኝበት ቦታ ከብዙ ሰዎች ጋር በአንድ ቤት መኖራቸው ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል።


የሮቤ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሳንባ በሽታ ስርጭት መከላከል አስተባባሪ ወ/ሮ ስኳሬ ንጉሴ እንደገለፁት ይህ በሽታ በብዛት ተሰራፍተዉ የሚገኘው ህዝብ በብዛት አንድ ላይ ተሰብስበዉ በሚኖሩበት አከባቢ እንደ ማረሚያ ቤት፣ፀበል ቦታ፣ መድረሳ አካባቢና መንገድ ላይ ተሰብስበው አንድ ላይ በሚኖሩ ሰዎች ላይ በብዛት ሊከሰት የሚችል መሆኑን ገልፀው ከከተማው ጤና ኤክስቴንሽን እና ከጤና ጣቢያ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ቀጣይነት ያለው ምርመራ እንደሚያካሄዱም ገልፀዋል።


በሌላ በኩል የTB በሽታ ዋና ዋና ምልክቶች ከሁለት እስከ ሶስት ሳምንት የሚቆይ የማያቀቋርጥ ሳል፣ የደረት ህመም፣ የሌሊት ላብ፣ ትኩሳት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ እና ያልታሰበ የክብደት መቀነስ መሆኑን የገለፁት በጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ከመድሃንት ጋር የተለመዱ TB ኃላፊ አቶ ማለዳ ገዛኽኝ ሲሆን ይህን በሽታ ለመለየት በዲጂታል X-Ray ምርመራ ለህግ ታራሚዎቹ ምርመራ እየተሰጠ መህኑን ገልፀዋል።


መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት

For More Information Use the following links:

Facebook: https://web.facebook.com/MaddaWalabuUniversityPages/

LinkedIn: https://www.linkedin.com/com.../madda-walabu-university-page

Telegram: https://t.me/Maddawalabubot

X/Twitter: https://x.com/MWU_University

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbCT1iYKbYMFSfNxOq1U

E-mail: info@mwu.edu.et

Event Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4

Related Articles

View All
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ከMSH Eliminate Project ጋር በመተባበር በጎባ ማረሚያ ቤት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ነፃ የሳንባ በሽታ ምርመራ እየሰጠ ይገኛል። | Madawalabu University