መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለ18ኛ ጊዜ አንድ ሺ ስድስት መቶ ሰባ ሶስት/1673/ ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ፡፡ዩኒቨርሲቲው በስምንት ኮሌጆች በተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ስር ያስተማራቸውን ተማሪዎቹን ነው በዛሬው እለት በደማቅ ሁኔታ ያስመረቀው፡፡
በጋሞ ዞን በጎርፍ እና መሬት መንሸራተት ምክንያት ህይታቸውን ያጡ ወገኖችን በማሰብ በተጀመረው የምረቃ ስነ-ስርአት ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የተከበሩ ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ለተመራቂ ተማሪዎች እና ወላጆች የእንኳን ደስ አላችሁ በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ በመልእክታቸው መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት እና ከህዝብ የተሰጠውን ተልእኮ ማለትም የመማር ማስተማር የጥናትና ምርምር እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራትን ከምስረታው አንስቶ ሲስራ እንደቆየ በመግለፅ ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ድረስ ከ47,500 በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁን አንስተው ዩኒቨርሲቲው በጤና ፣በግብር፣ በቱሪዝም እና በብዝሃ ህይወት ጥበቃ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በርካታ ጠቃሚ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ክቡር ፕሬዝዳንቱ አክለውም ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ሚኒስቴር የተደረገውን ሪፎርምን ተከትሎ በተቋሙ ከ2018ዓ.ም መጀመሪ አንስቶ ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ስራዎች በማከናወን ላይ እንደሚገኝም በመግለፅ ተመራቂ ተማሪዎች ወደ ስራ ሲሰማሩ በቤተሰቦቻቸውን እና ሀገራቸውን በተሰማሩበት ሙያ በማገዝ የተሰጣችሁን አደራ በታማኝነት እንድትወጡ መልእክታቸውን አስተላለፈዋል፡፡
በምረቃው ላይ የተገኙት የእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አማካሪ ሚኒስቴር ዲኤታ የተከበሩ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ህይወት በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ እንዳሉት የአንድን ሀገር እድገት እና ብልፅግና ምሰሶ ከሆኑት ተቋማት ውስጥ ዋነኛው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ናቸው ብለዋል፡፡ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲም በመንግስት የተሰጠውን የመማር ማስተማር፣ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች አቀናጅቶ ስለመስራቱ የዛሬዎቹ ተመራቂዎች ማሳያ ናቸው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
በምረቃ ስነስርአቱ ላይ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ምክትል የቦርድ አመራር ሰብሳቢ ፕሮፌሰር በላይ ስምአኒ፣ ዶ/ር አብዱልአዚዝ ዳውድ የብልፅግና ፖርቲ ስራ አስፈፃሚና የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ፣ባሌ ዞን አስተዳደር አቶ አብዱልሀኪም አልዩ ፣የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ዲኖ አሚን እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡
በፕሮግሙ ማጠቃለያም ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተመራቂዎች ሜዳሊያ እና የዋንጫ ሽልማት ከክቡራን እንግዶች እና ከክቡር ፕሬዝዳንቱ እጅ ተረክበዋል፡፡
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት
For More Information Use the following links:
Facebook: https://web.facebook.com/MaddaWalabuUniversityPages/
LinkedIn: https://www.linkedin.com/com.../madda-walabu-university-page
Telegram: https://t.me/Maddawalabubot
X/Twitter: https://x.com/MWU_University
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbCT1iYKbYMFSfNxOq1U
E-mail: info@mwu.edu.et
Event Gallery


















