ዩኒቨርሲቲው በአካዳሚክ ዘርፍ፣ በአስተዳደር ዘርፍ እና ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ዘርፍ እንዲሁም በጎባ ጤና ሳይንስና ህክምና ኮሌጅ እና በሻሸመኔ ካምፓስ ላለፉት 6 ወራት ሲሰሩ የቆዩ ስራዎች ቀርበው በካውንስል ዓባላት ተገምግመዋል።
የካውንሉ ዓባላት በቀረበው ሪፖርት ላይ በርካታ ጥያቄ እና ሃሳብ ያነሱ ሲሆን፣ በዘርፉ አመራሮች ሃሳብ እና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና የሥራ አፈፃፀም ግምገማውን የመሩ ሲሆን በግምገማው ሥነ-ሥርዓት ላይ መዝጊያ ባደረጉት ማጠቃለያ ተቋሙ በለውጥ ውስጥ መሆኑን አመላክተው በዩኒቨርሲቲው በየሥራ ክፍሎች ባለፉት 6 ወራት ካከናወንናቸው ተግባራት ከተረካከብናቸው ቁልፍ ውጤት አመልካቾች ( KPI) አንፃር የተከናወኑና ያልተከናወኑት ተግባራት ተለይተው የተገመገሙበት፣ ስራዎቹ በመሰራታቸው የመጣው ለውጥና ተፅኖ እንዲሁም የትኛው ዘርፍ እና የሥራ ክፍል በታለመውና በታቀደው አግባብ ተልዕኮውን እየተወጣ እንደለ በመለየት ፣ በሂደቱም ጠንካራና ቁርጠኛውን አመራር ከለዘብተኛው ለመለየትና ለተሻለ ተቋማዊ ለውጥ ለማቀድ እድል ፈጥሮልናል ብለዋል።
Event Gallery












