በዩኒቨርስቲው ሲያ ገለግሉ የነበሩ የተማሪዎች ሕብረት የአገልግሎት ግዜያቸው ስለተጠናቀቀ አዲስ የሕብረቱ አመራር ምር ጫ መደረግ ግድ መሆኑን የገለፁት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዲን አቶ ተስፋዬ ዘውዴ፣ የተማሪዎች ሕብረት ምርጫን በመከተል ምርጫው እንዲደረግ ቅድመ-ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰዋል።
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የተከበሩ ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና በምርጫው ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ የተማሪዎች ሕብረት አመራር ምርጫ አካታች፣ ነፃ፣ ገልተኛ እና ዴሞክራሲያዊ መሆን እንደለበት ጠቅሰው፣ ተመራጮች በሥነ-ምግባራቸው ምስጉን፣ በትምህርታቸው ጠንካራ እንዲሁም ሁሉንም በአንድ ዓይን የሚያዩ መሆን እንዳለባተውም መክረዋል። ለተሰናባች የተማሪዎች ሕብረትም ምስጋና አቅርበዋል።
በተደረገው ምርጫም ተማሪ ኢፍራ ጪሮ የተማሪዎች ሕብረት ፕሬዚዳንት፤ ተማሪ ፊራንቦን ደጀኔ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም ተማሪ ጀማል ነገዎ የሕብረቱ ዋና ጸሐፊ ሆነው በአብላጫ ድምፅ የተመረጡ ሲሆን፣ በሕብረቱ ካውንስል ዓባላት ፊት ቃለ-መሃላ ፈፅመዋል።
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር በዛብህ ወንድሙ ከምርጫው መርሃ-ግብር ብኋላ ለተማሪዎች ካውንል ባደረጉት ንግግር፣ በተቋሙ ውስጥ የመማር-ማስተማር ስራን ለማሳለጥ የተማሪዎች ሕብረት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፣ በተማሪዎች እና በማኔጅመንቱ መኃል ድልድይ በመሆን እና የተማሪዎችን ችግሮች በፍጥነት ለይተው መፍትሔ እንዲሰጥበት የተሻለ ስራን እንዲሰሩ አቅጣጫ ሰተዋል።
Event Gallery















