በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ  ባሉት ክፍት የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የተመዘገቡ እጩ ተወዳዳሪዎች ውጥን እቅዳቸውን ለዩኒቨርስቲው ሴኔት አቀረቡ

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ባሉት ክፍት የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የተመዘገቡ እጩ ተወዳዳሪዎች ውጥን እቅዳቸውን ለዩኒቨርስቲው ሴኔት አቀረቡ

Feb 16, 2026

በሶስቱም ካምፖሶች በተለያዩ የአካዳሚክ ክፍት የኃላፊነት ቦታዎች በወጣው ማስታወቂያ መስፈርቱን አሟልተው የተመዘገቡ እጩ ተወዳዳሪዎች ውጥን እቅዳቸውን ለዩኒቨርስቲው የሴኔት ዓባላት አቀረቡ።


በሥነ- ስርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጊት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የተከበሩ ዶ/ር ብርሃመስቀል ጠና ሲሆኑ የአካዳሚክ ኃላፊነት ቦታዎች በትክክለኛ በለሙያ እንዲመራ ለማድረግ በእውቀት፣ ክህሎትና ችሎታ እንዲሁም የተሻለ የትምህርት ዝግጅትና ቁርጠኝነት ያላቸውን መምህራን ወደ ኃላፊነት ቦታ የሚመጡበት ስርዓት ስለሆነ፣ የተከበረዉ ሴኔት በገለልተኝነት የእጩ ተወዳዳሪዎች ውጥን እቅድ እንዲገመግሙ አጽኖት ስተዋል።


የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር በዛብህ ወንድሙ በበኩላቸው፣ ሶስቱም ካምፓሶች ውድድር የሚደረግባቸው የአካዳሚክ ኃላፊነት ቦታዎች እጅግ በጣም ወሳኝ በመሆናቸ፣ በእጩ ተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ ውድድር እንደሚጠበቅ አንስተው፣ ለዚህም ውጥን እቅዶቻቸውን በግልፅ ለሴኔት ዓባላት ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።


በሁሉም ለውድድር በወጡት የአካዳሚክ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ እጩ ተወዳዳሪዎች ውጥን እቅዶቻቸውን አቅርበው በሴኔት ዓባላት ተገምግሟል።


Event Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8
Gallery image 9
Gallery image 10
Gallery image 11

Related Articles

View All