በዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና የተመራ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የካውንስል አባላት የዩኒቨርሲቲውን የተለያዩ ክፍሎችን የስራ እንቅስቃሴ (Management by Walk Around) በመዘዋወር ምልከታ አደረገ::
የምልከታውም ዋና ዓላማ ፕሬዚዳንቱ ሲያስረዱ የስራ ሀላፊዎች ረዥም ጊዜያቸውን በቢሮ ውስጥ በመቀመጥ ብቻ የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት አዳምጦ ከመገምገም ባሻገር በተጨባጭ የተከናወኑ ተግባራት በመሬት ላይ ስለመኖራቸው ለመገንዘብ ያስችላል ብለዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ሰዎች በሥራቸው ላይ እያሉ ውይይት ማድረግ ፣ መስተካከል ስለሚገባቸው ነገሮች ወዲያውኑ ባሉበት እንዴት፣ በማንና መቼ መስተካከል እንዳለባቸው ለማመላከት፣ አንዱ ክፍል ከሌላው እንዲማር ለማድረግ፣ ቀጥተኛና በቦታው ላይ ወዲያው ግብረ-መልስ ለመስጠት እንደሚያስችልም ጨምረው አስረድተዋል፡፡
በዛሬው የመስክ ምልከታ ከተደረገባቸው የተለያዩ የስራ ክፍሎች ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ ፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ፣ የተማሪዎች ክሊኒክ ፣ የመማሪያ ክፍሎች ፣ የህግ ት/ቤት ምስለ ችሎት ፣ የአይ ሲቲ ክፍሎችና የሴት ተማሪዎች ልዩ የማጥኛ ክፍሎች ይገኙበታል፡፡
በእያንዳንዱ ክፍሎች በተደረገው የመስክ ምልከታ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንትና የካውንስል አባላት የታዩትን ክፍተቶች በተገቢው ሁኔታ በግልፅ ያመላከቱበትና ጠንካራው ጎን ደግሞ የበለጠ እንዲጠናከር ገንቢ ሀሳቦች በሰፊው ተሰጥቶበታል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ተቋም በጋራና በመተባበር የሚገነባ መሆኑን በሚገባ ያሳዩበትና ለእያንዳንዱ የስራ ክፍል ሀላፊነት በመስጠት የታዩ ክፍተቶች የሚስተካከሉበት፣ ሁሉም ሰው የተሰጠውን ሀላፊነት በባለቤትነት ስሜትና በሀላፊነት ሲወጣ የተቀሙን ራእይና ተልእኮ ማሳካት እንደሚቻል አስምረውበታል፡፡
በማጠቃለያም ፕሬዝዳንቱ ይህ አሰራር በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስገንዝበዋል።
የምልከታው ተሳታፊ የዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላትም ከዚህ ምልከታ ለየሥራ ክፍሎቻቸው ብዙ የተማማሩበት ፣ ትኩረት በመነፈጋቸው ችግር ሆነው የቀጠሉ ነገር ግን ደግሞ ቀርበን ስናይ በቀላሉ መለወጥ የሚችሉ በርካታ ጉዳዮች እንደነበሩ የተረዱበት አይን ከፋች አካላዊ ምልከታ ፕሮግራም እንደነበረና ዛሬ በተቀመጠው አቅጣጫና አመራር ሁሉም በወሰደው የቤት ሥራ በአግባብ በመወጣት ቢያንስ ዛሬ ያየናቸው ችግሮች ችግር ሆነው እንዳይቀጥሉ ለማስቻል መግባባት የተደረሰ ሲሆን ይህ ዓይነት ፕሮግራም መቀጠል ያለበት መሆኑን ፤ በጋራ ጥረትም የተያዘውን የለውጥ ሥራ እውን ማድረግ እንደሚቻል በመግለጽና በመስማማት የእለቱ የስራ ክፍሎች ምልከታ ተጠናቋል፡፡
Madda Walabu University Council Members Conduct On-the-Job Supervision to Strengthen Institutional Operations.
The Madda Walabu University Council Members, led by Dr. Berhanemeskel Tena, President of the University, conducted an on-the-job supervision visit to support and strengthen the day-to-day operations of middle- and frontline management bodies.
The primary objective of the supervision was to promote the leadership approach of Management by Walking Around (MBWA), enabling the Council and University leadership to observe ongoing activities, assess performance across various offices, and provide immediate, practical, and actionable feedback. The visit also provided an opportunity to evaluate progress made to date, identify gaps, enhance operational efficiency, and share best practices across different management levels.
On the first day, the supervision covered the College of Social Sciences and Humanities, College of Business and Economics, Students’ Clinic, classrooms, the Law School Moot Court, ICT facilities, and the Girls’ Special Study Centers.
During the visits, the President and Council Members delivered constructive feedback and guidance aimed at improving institutional performance and fostering collaborative efforts to achieve the University’s mission and vision, ultimately serving the broader needs of the nation.
In his concluding remarks, the President emphasized that this supervisory culture should be institutionalized across all management levels to ensure effective service delivery to students, staff, and stakeholders. The Council Members also committed to strengthening trust among managers, enhancing communication and motivation, and conducting regular monitoring and evaluation of university activities.
Event Gallery

















