በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የ2018 የከፍተኛ ትምህርት የስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡
በሥነ-ስርዓቱ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የጂማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባ ፊጣ ስፖርት ለሁለንተናዊ አንድነት፤ወዳጅነትና ፍቅርን በመስበክ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አንስተው፤ዝግጅቱ እንዲሳካ ያለሰለሰ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ማሕበር ፕሬዝዳንት አቶ አባይ በላይሁን በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስፖርትን ከሰው ልጅ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ጋር በማያዝ እና በስፖርት ዙሪያ ኢንቨስትመንትን፣ ጥናትና ምርምርን በማስፈት፤ ጤናማ እና ሁሉን አቀፍ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
የኢፌዲሪ የባህልና ስፖርት ሚኒቴር ሚኒስተር ዴኤታና የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ መኪዩ መሐመድ ባደረጉት ንግግር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እውቀትና ክህሎት ከማሳለጥ ጎን ለጎን ጤናማ፤ ብሩህ፤የተወዳጀ ማንነት በማህበረሰብ መካከል የሚፈጠርበት ቦታ መሆኑን ገልፀው፤ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ትልቁ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ውድድሩ በ15 የስፖርት አይነቶች በ48 ዩኒቨርስቲዎች መካከል የሚደረግ ሲሆን፤ በውድድሩ ከ4500 በላይ ተማሪዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
በመክፈቻው በተደረገው የወንዶች የእግር ኳስ ውድድር አዘጋጁ ጂማ ዩኒቨርስቲ 5 ለ 0 ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲን የረታ ሲሆን፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 1 ለ 0 አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክሎሎጂ ዩኒቨርስቲን አሸንፏል፡፡
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብእና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት
Event Gallery











