በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ውድድር ላይ በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲን ወክለው ለሚሳተፉት ልዑካን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሽኝት ተደረገላቸው።
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የተከበሩ ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና በፕሮግራሙ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ስፖርት ፍቅርና አንድነትን በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው በማስታወስ በ2018ቱ ሀገር አቀፍ ስፖርት ፌስቲቫል ውድድር ላይ ዩኒቨርሲቲያችንን በመወከል የሚወዳደሩ ተማሪዎቻችን የስፖርታዊ ጨዋነትን በመላበስ፤ በአንድነት በመስራት ውድድሩን ለማሸነፍ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው ያሳሰቡት ፕሬዚዳንቱ ተወዳዳሪዎቻችን በሚወዳደሩበት የስፖርት አይነቶች በማሸነፍ የዩኒቨርስቲያችንን ዓርማ ከፍ እንደሚያደርጉ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል ።
በመጨረሻም የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች ለልዑካን ቡድኑ ተወካዮች የኢትዮጵያ ባንድራን እና የዩኒቨርሲቲውን አርማ ከአደራ ጋር አሰረክበዋቸዋል።
Event Gallery













