የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በስንዴ ምርጥ ዘር ብዜት ላይ በመሰማራት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ማህበራዊ ኃለፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ዩኒቨርቲው ከመማር ማስተማር፤ ጥናትና ምርምር ጎን ለጎን ከሚሰራቸው ማህበራዊ አገልግሎቶች አንዱ የሆነው፤ በአከባቢው ሊላመዱ እና ከፍተኛ ምርት ሊያስገኙ የሚችሉ በጥናት የተደገፉ ቦኩ የሚባል የስንዴ ምርጥ ዘር ምርቶችን በማባዛት ለአከባቢው አርሶ አደሮች በመስጠት በኩታ ገጠም እርሻ ማልማተቸው ይታወቃል፡፡
በዚህ የምርት ወቅትም ዩኒቨርሲቲው ቦኩ እና ቁሉምሳ የሚባሉ የስንዴ ምርጥ ዘሮች በማባዛት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ማህበራዊ ኃለፊነቱን በሚገባ እየተወጣ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቄላ፤ ጎመን ዘር፤አተር እና ሌሎች የእህል ዘሮች በጥራት በማምረት ለአርሶ አደሮች ልምድ በማስተላለፍ ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት ላይ ነው፡፡
በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ፤የምርምር፤ማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር በዛብህ ወንድሙ የስንዴ ምርጥ ዘር ብዜት ሂደት ላይ እያለ በቦታው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ከዩኒቨርሲቲው የትኩረት አቅጣጫ አንዱና ዋነኛው ግብርና ስለሆነ ዩኒቨርሲቲው ግብርና ላይ በተለየ መልኩ ትኩረት ሰቶ በመስራት ላይ ይገኛል ብለው፤ በአከባቢው የሚገኝ የምርጥ ዘር ማበጠሪያ ማሽን ከሲኮ መንዶ ዩኒየን ጋር በመሆን በዚህ የምርት ወቅት 260 ኩንታል ቦኩ እና 79 ቁሉምሳ የተባለ ምርጥ የስንዴ ዝሪያ ማዘጋጀታቸውን ተናግረው፤ የተዘጋጀው ምርጥ ዘር በመጪው የምርት ዘመን አርሶ አደሮች በማሳቸው ላይ በኩታ ገጠም እንዲያባዙት የሚሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህ የምርት ዘመን ዩኒቨርሲቲው በሶስት የተቀናጀ የምርመር ጣቢያ እና በሰባት ወረዳዎች በአርሶ አደሮች ማሳ በኩታ ገጠም የዘር ብዜት እያከናወነ መሆኑ የታወሳል፡፡
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት
Event Gallery

















