የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በትጋት እየሰራ ይገኛል

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በትጋት እየሰራ ይገኛል

Feb 04, 2026

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የገበሬውን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የምርጥ ዘር ብዜትን በጥናትና ምርምር በተደገፈ መልኩ በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡ዩኒቨርሲቲው በ2016ዓ.ም ከኢትዮጵያ የግብርና ግብአቶች ቁጥጥር እና ምርት ባለስልጣን ባገኘው ፍቃድ መሰረት በአሁኑ ወቅት የቁልምሳና ቦኩ ምርጥ ዘር ብዜትን በማከናወን ምርቱን በመሰብሰብ ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ሁለት ምርጥ የባቄላ ዝርያዎችን (ዶሻ እና ጎራ) በተመሳሳይ ሁኔታ እያመረተ ይገኛል፡፡


የተመረተውን ምርጥ ዘር የዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት አባላት (የአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልገግሎት ም/ፕ ዶ/ር በዛብህ ወንድሙ እና የእሰተዳደርና ልማት ም/ፕ ኢሳ ሀሰን (ረዳት ፐሮፌሰር))፣የግብርና ኮሌጅ ባለሙያዎች፣የዩኒቨርሲቲው ገቢ ማመንጫ እና ሌሎችም በቦታው ተገኝተው የምርት አሰባሰቡን በመደገፍና በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ 


በምርት አሰባሰቡ ቦታ ላይ የተገኙት የመወዩ መምህርና ተመራማሪ እንዲሁም የምርጥ ዘር ብዜትና ስርጭት አሰተባባሪ አቶ ድርባ ተስፋዬ እንደገለፁት ምርቱን በክላስተር ለተደራጁት ገበሬዎችና ለሌሎችም በማሰራጨት ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ እንደታሰበ ገልፀውልናል፡፡ከዚህም ባሻገር ዩኒቨርሲቲው ሀገራችን በምግብ ሰብል እራሷን ከመቻል አልፋ ለሌሎችም ለመትረፍ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ወሳኝ ሚና ለመወጣት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት

Event Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8
Gallery image 9

Related Articles

View All